አፍሪቃና ዴሞክራሲን የመትከል ጥረቷ በ2015ዓም
ኮንጎ ብራዛቪል፣ ከ30 ዓመት በኋላም በስልጣን የመቆየት ፍላጎት
ዴኒ ሳሱ ንጌሶም ለተጨማሪ የስልጣን ዘመን ሁኔታዎችን አመቻችተዋል። የ72 ዓመቱ ፕሬዚደንት እጎአ ከ1992 እስከ 1997 ዓ,ም በስተቀር ኮንጎ ብራዛቪልን ከ30 ዓመት በላይ በመምራት ላይ ናቸው። የሃገሪቱን መሪ የስልጣን ዘመን በሚመለከተው የሕገ መንግሥቱ አንቀጽ ላይ በተደረገው ማሻሻያ ላይ ባለፈው ጥቅምት ወር በተካሄደው ሕዝበ ውሳኔ ወቅት ደም አፋሳሽ ሁከት ቢፈጠርም፣ በይፋ የወጡ ውጤቶች እንዳሳዩት፣ ማሻሻያው የሰፊውን ሕዝብ ድጋፍ አግኝቶዋል። የተቃውሞ ቡድኖች ውጤቱን የተጭበረበረ ነው በሚል አልተቀበሉትም። የጎረቤት ዴሞክራቲክ ኮንጎ ሬፓብሊክ ሕዝብም ፕሬዚደንት ጆሴፍ ካቢላ በያዙት ተመሳሳይ እቅድ አንፃር ተቃውሞ ጀምሮዋል።